ከ10,000 ወደ 2 ሚሊዮን ዶላር ፤ በ27 ዓመቷ!
አስር ሺህ ዶላር ብቻ ነበራት... በአራት አመታት ውስጥ ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር አሳደገችው! ይህ የማይታመን ታሪክ የአንዲት ወጣት ሴት ሲሆን፣ በድፍረትና በፅናት የተሞላ ጉዞዋ ልክ እንደ አድዋ ጀግኖች አኩሪ ገድል ያስገርማል። በተማሪ ብድር ዕዳ የተተበተበች፣ የወር ደሞዟ እንኳን አልበቃ ብሏት ከእጅ ወደአፍ የምትኖር ነበረች። ሆኖም ግን በውስጧ የነበረው እሳት አልጠፋም። አንድ የስራ ባልደረባዋ የሰጣት ቀላል ምክር ህይወቷን ለዘለዓለም ቀየረው። በስቶክ ማርኬት ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ያቀረበላት ጥቆማ ልክ እንደ አድዋ ላይ የተተኮሰው የመጀመሪያ ጥይት ነበር - የነፃነት ጥይት! ይህች ሴት ማን ናት? እንዴትስ ይህን አስደናቂ ስኬት ማስመዝገብ ቻለች? ሚስጥሯን ለማወቅ እና እርስዎም ወደ ፋይናንሺያል ነፃነት ጎዳና መጓዝ ለመጀመር ዝግጁ ነዎት? ታሪኳን ማንበብዎን ይቀጥሉ... እና አድዋ ትራንስፎርሜሽን ሴንተር ወደሚያቀርበው የኢንቨስትመንት አለም ውስጥ ይግቡ!
By Adwa Transformation
9/15/20241 min read
ቲፋኒ ጄምስ፣ ልክ እንደ ብዙ አዲስ የኮሌጅ ተመራቂዎች፣ በተማሪ ብድር የተነሳ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ተሸክማ ነበር፤ የወር ደሞዟ እያጠራት በእጅጉ ተቸግራለች። ነገር ግን በውስጧ ያ የማይበገረው የሠው ልጅ መንፈስ፣ ያ አድዋ ላይ ድል ያስገኘው የጀግንነት ስሜት ይንቦገቦግ ነበር። "አንድን ነገር በጥልቀት ከተረዳህ ፍርሃት የለም" እንዲሉ አበው፤ እሷም የገንዘብ ዓለሙን በጥልቀት ለመረዳት ጓጓች።
አንድ ቀን እኤአ በ2019 የሥራ ባልደረባዋ የአንድ ወር ደሞዟን በሙሉ በቴስላ አክሲዮን ላይ እንድታፈስ ሐሳብ አቀረበላት። በወቅቱ የቴስላ አንድ አክሲዮን ዋጋ ከ60 እስከ 70 ዶላር አካባቢ ነበር።
"ያኔ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኢንቨስትመንት የተማርኩት" ትላለች። ይህ የመጀመሪያ እርምጃ የአድዋን ድል አድራጊ መንፈስ በውስጧ ይበልጥ ቀሰቀሰ። እንደ አድዋ ጀግኖች ሁሉ እሷም በራሷ መንገድ ድል ማድረግ እንደምትችል እምነት ሰነቀባት።
"መጀመሪያ ላይ በጣም ፈራሁ። ነገር ግን እንደ ጦር ሜዳ ጀግኖች ድፍረት ካላሳየሁ እድሉን አጣለሁ ብዬ አሰብኩ" ትላለች ጄምስ።
በዚህ ድፍረት ተነሳስታ ወደ ገበያው ገባች። ነገር ግን ያለ ዕውቀት እና ዝግጅት አልነበረም። በርካታ መጻሕፍትን አነበበች፣ የኢንቨስትመንት ሴሚናሮችንና ስልጠናዎችን ተከታተለች፣ ልምድ ካላቸው ባለሀብቶችም ምክር ጠየቀች።
በረጅም ጊዜ እውስጥ የሚያድጉ ኩባንያዎችን ፣ በS&P SPDR የአክሲዮን ገበያ ፈንድ (ETFs) እና በሴሚኮንዳክተር ቺፕ አክሲዮኖች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ጀመረች።
“ታዲያ ውጤቱስ?” ብላችሁ መጠየቃችሁ አይቀርም። በአጭር ጊዜ ውስጥ የ10,000 ዶላር ኢንቨስትመንቷ ወደ 2 ሚሊዮን ዶላር አድጓል! ልብ ይበሉ፤ ይህ ሁሉ የሆነው እንግዲህ በአራት አጭር ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው!
ነገር ግን ይህ ስኬት በቀላሉ የመጣ አልነበረም። ጄምስ የጃማይካ እና የሄይቲ ስደተኞች ልጅ ስለነበረች በአክሲዮን ገበያው ዓለም ውስጥ እራሷን እንደ እንግዳ ትቆጥር ነበር። “ይህ የስቶክ ማርኬት ዓለም በአብዛኛው በ"ከፍተኛ ዲግሪ" ባላቸው ነጮች ወንዶች የተሞላ ነው። ለእኛ ለጥቁሮች ስቶክ ማርኬት ብዙም የማይነሳ ርዕስ ነበር። በጣም አስፈሪ ነው፤ የአክሲዮን ገበያው የራሱ የሆነ ልዩ ቋንቋ ስላለው ለመረዳትም አስቸጋሪ ነው" ትላለች:::
ነገር ግን ጄምስ ተስፋ አልቆረጠችም። በትጋት ተምራለች፣ ከስህተቶቿ ተምራለች፣ እና በየጊዜው እራሷን አሻሽላለች። ከድል አድራጊነት ተሞክሮዋ በመነሳት እንዲህም ትላለች፤ “ አሁን ላይ የተማሪ ብድር ዕዳዬን ከፍያለሁ፣ እናቴን ከኪራይ ቤት አውጥቼ ለራሷ ቤት ገዝቸላታለሁ። ይህ ሁሉ የተቻለው በኢንቨስትመንት አማካኝነት ነው። ይህንን ስኬት ለማግኘት ቁልፉ ትምህርት፣ ድፍረት እና ትጋት እንደሆነ ታምናለች።"
ዛሬ ጄምስ የፋይናንስ ነጻነቷን አግኝታለች። ይህ ሁሉ የጀመረው ግን በአንዲት ትንሽ እርምጃ ነበር - ልክ እንደ አድዋ ላይ የተተኮሰችው የመጀመሪያዌ ጥይት። ጄምስ ታዲያ ለጀማሪዎች ሶስት ወሳኝ ምክሮችን ታካፍላለች፦
ተዘጋጁ
“የዓለም ጦርነቶች፤ የዋጋ ግሽበት እና የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ገበያውን እያናወጡት ቢሆንም፣ ምርጡ ጊዜ ገና አላለፈም። ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች በኋላ ሁሌም የመልሶ ማገገም እድል አለ።"
ስለ ገበያው መሰረታዊ ነገሮች ይረዱ፣ ቁልፍ የድጋፍ እና የተቃውሞ ደረጃዎችን ለመለየት የቴክኒካል ትንተና ስልትን ይማሩ፣ እና ጥሩ መሰረት ባላቸው ኩባንያዎች ላይ ያተኩሩ።
ሰፊ አድማስ ይኑርዎት
"የሚያውቋቸውን ኩባንያዎች ብቻ አይከተሉ። ለምሳሌ አፕልን ከወደዱ፣ ከአፕል ባሻገር ይመርምሩ። እንደ ስማርት ስልኮች ያሉ ተወዳጅ ምርቶችን ለመገንባት የሚያገለግሉ ሌሎች ግብአቶች አሉ። ቺፖች በጣም ጥሩ ናቸው" ትላለች።
አይፍሩ
"እኛ ሴቶች በየቀኑ ከሚገጥሙን ነገሮች ጋር ሲነጻጸር የአክሲዮን ገበያ ፍርሃት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም" ትላለች ጄምስ።
ሀብት ለመገንባት፣ "ኢንቨስት ማድረግ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው" ስትል አበክራ ትናገራለች። በስቶክ ማርኬት ውስጥ ገንዘብ ማግኘት ወደ ሰፊ የፋይናንስ ነፃነት ለመግባት ብሎም በራስ ለመተማመን በር ይከፍታል፤ የምትፈልጉትን ለማድረግ ነጻነትን ይሰጣችኋል። የምንፈልገውን ዓይነት ምርጥ ህይወት መኖር እንችላለን" ስትል በልበ ሙሉነት ታበስራለች።
እርስዎስ እንደ ጄምስ ፈር ቀዳጅ መንፈስ በውስጥዎ አለ? የፋይናንስ ነጻነትዎን በኢንቨስትመንት ማግኘት ይፈልጋሉ? በአድዋ ትራንስፎርሜሽን ማዕከል የሚሰጠውን አለም አቀፍ የስቶክ ገበያ ስልጠና ይቀላቀሉ። እውቀት ኃይል ነው፤ ይህ እውቀት የፋይናንስ ህይወትዎን እንዲያብብ ያደርጋልና። ዌብሳይታችንን በመጎብኘት ዛሬውኑ ይመዝገቡ! https://adwatransformation.com
ምንጭ :- CNBC